anchu

አቶ ካንቹላ ካንቤ


የሲዳማ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

መልዕክት

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 28/2015 ዓ.ም መሰረት የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡ ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ሥራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በአዋጅ ከተሰጡት ኃላፊነቶች አንዱና ዋነኛው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ውጤታማ፣ ትርፋማ፣ ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ እንዲሆኑ ለመስቻል አጠቃላይ የልማት ድርጅቶችን የሥራ እንቅስቃሴና ለማሳለጥ የአሠራር ሥርዓትን ዘርግቶ በበላይነት መከታተል፣ መደገፍና መቆጣጠር ነው፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማ በማድረግ ረገድ ባለስልጣን መ/ቤታችን ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየሰራ ያለ ሲሆን በዋናነት የክልሉን ሁሌንተናዊ ዕድገት ማፋጠን ብሎም አገራዊ ዕድገት ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት፣ ዜጎችን በልማት፣ በትምህርት፣ በማህበራዊ አገልግሎት፣ በሥራ እድል ፈጠራ፣ የገበያ ክፍተትን መሸፈንና መሙላት፣ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት ወዘተ ሥራዎች ትኩረት ተደርጎ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በቀጣይም ባለስልጣን መ/ቤታችን የልማት ድርጅቶችን ትርፋማና ተወዳዳሪ ለማድረግ አዳድስ የአሠራር ሥርዓቶችን በመዘርጋትና የተለያዩ መመርያዎችን በማውጣት ተወዳዳሪነታቸው እንዲጨምርና የተቋቋሙበትን ዓላማ ማሳካት እንዲችሉ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል፡፡

አቶ ካንቹላ ካንቤ ዳሣ
ዋና ዳይሬክተር


ተጨማሪ ለማንበብ