አገልግሎቶች | የሲዳማ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን


የሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት


ዳይሬክቶሬቱ የሚሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች:-
  • የተቋሙን ሠራተኞች መንግሥት ባወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ የማድረግ አገልግሎት
  • በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃ አገልግሎት
  • አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ የማድረግ አገልግሎት
  • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት ስልጠና መስጠት
  • ለመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና እንድያገኙ የማድረግ አገልግሎት
  • የተለያዩ የድጋፍ ደብዳቤዎችን የመስጠት አገልግሎት
  • ጡረታ ለሚወጡ መንግስት ሰራተኞች ሁኔታ የማመቻቸት አገልግሎት
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ የማድረግ አገልግሎት
  • መልካም ተሞክሮዎችን በማጣጣም ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበትን አዳዲስ አሰራሮች በመቀመር ማስፋፋት
  • የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮችና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን የመከታተል አገልግሎት
  • ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችና አገልግሎቶች ሳይዛቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ የማድረግ አገልግሎት
  • የሠራተኞች የግል ማህደሮች ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ ክትትል የማድረግ አገልግሎት
  • የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ማድረግ
የዳይሬክቶሬቱ የሰራተኛ ደረጃ:-
የዳይሬክቶሬቱ ስም የሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት
የሰራተኞች ብዛት (ወንድ) ___
የሰራተኞች ብዛት (ሴት) ___
አጠቃላይ ሰራተኞች ብዛት ___