ተልዕኮ
የገበያ ክፍተትን ለመሙላት ቀደም ብለው የተቋቋሙና ወደፊትም የሚቋቋሙ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ግልጽ የኮርፖሬት አስተዳደርና ፋይናንስ ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ የቴክኖሎጅና የማስፈፀም አቅም እንዲፈጥሩና ትርፋማ እንዲሆኑ በማድረግ የክልሉን ሁለንተናዊ ልማት እንዲደግፉ ማስቻል ነው፡፡
ራዕይ
በ2030 ዓ.ም ስትራቴጂክ የሆነ አመራር በመስጠት የክልሉ የመንግስት ልማት ድርጅቶች በሀገር አቀፍና በአፍርካ ደረጃ በገበያው ተወዳዳሪ፣ ትርፋማና ተመራጭ ሆነው ማየት፣
እሴቶች
- ለልማት ድርጅቶች ስኬት እንተጋለን፡፡
- ምንጊዜም ለመማርና ለለውጥ ዝግጁ ነን፡፡
- ለፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግርና ተጠቃሚነት እንሰራለን፡፡
- ቅንጅታዊ አሰራርን እንተገብራለን፡፡
- ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እናሰፍናለን፡፡
- በውጤት መለካት እናምናለን፡፡
- ፈጣን ምላሽና ጥራት ያለው አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
- የህግ በላይነትን እናከብራለን፡፡
- የፈጠራና የምርምር ስራዎችን እናበረታለን፡፡
- ቅን፣ ታማኝና ቁርጠኛ ሆነን እንሰራለን፡፡


